ጌቴሴማኒ Gethesemane

Regular price $10.00 Sale price $7.00
/

Only -12 items in stock!

ይህ መፅሐፍ በአይነቱና በይዘቱ ለየት ያለ ዜማዊ መፅሐፍ ነው። ፀሃፊው ጌቴሴማኒ ከተሰኘው የዝማሬ አልበሙ በመነሳት ብዙ ባልተለመደ መልኩ የዝማሬዎቹን ውስጣዊ ሚስጢር ፈልቅቆ በማውጣት መዝሙሮቹን ለሚያዳምጡ ሁሉ ዘማሪው በምን መነሻነት እና በምን አይነት ስሜት እንደዘመራቸው የሚያስረዳ ነው። መጽሐፉ የዝማሬዎቹን ሚስጢራት ከመግለጥ ባለፈ ህይወትን የሚመረምር በእግዚአብሔር ቃል የተቀመመ ነው። በማስተዋል ለሚያነቡት ራስን በእግዚአብሔር ፊት ለማየት የሚረዳ በየትኛውም የክርስትና እና የአገልግሎት ደረጃ ብንሆንም ወደ ንስሃ የሚመልስ ግሩም መፅሐፍ ነው። የዝማሬዎቹን መንፈሳዊ መነሻ አውድና ሐሳቦች ከመግለፅ ባሻገር መፅሐፉ በራሱ የሚያንፅና አስተማሪ ነው። በውስጡም ያሉት ሐሳቦች ጠለቅ ያሉ መንፈሳዊ ግንዛቤ የሚሰጡ ብቻ ሳይሆኑ ወደ ጌታ ልብ የቀረቡና የመቅረብንም ፍላጎት የሚያነሳሱ ናቸው። እርሶም ይህን መፅሐፍ በማንበብ በውስጡ ያለውን ሰማያዊ መና ይመገቡ።


Recently viewed